Back

Trade name registration

የአገልግሎቱ አጭር መግለጫ

በሚኒስቴር መስራቤቱ የዋና ምዝገባያካሄዱና በዚሁ መሰረት  የንግድ ስራ ፈቃድ የተሰጣቸው ነጋዴዎችየንግድ መደብሮቻቸውን የሚሰይሙአቸው የንግድ ስሞች ስለመመዝገቡ የሚሰጥ የባለቤትነት ማስረጃ ነው።

የንግድ ስም አንድን የንግድ ተቋም ከሌላው ለመለየት የሚያገለግል መለያ ነው፡፡

የንግድ ስም የንግድ ስራ ስም እና የባለቤት ስም በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡

የንግድ ስራ ስም ፦ ማለት አንድ የንግድ ተቋም የሚለይበት ዘዴ በህጋዊነት የሚንቀሳቀስበት አግባብ ማለት ሲሆን የንግድ ስራ ስምን ለመጠቀም በህግ ከተደነገገ አካል ስሙን በማስመዝገብ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

የባለቤት ስም ፦ ማለት በዜግነት መታወቂያ ወረቀቱ ላይ የተቀመጠውን ስም በመጠቀም ቀጥታ የንግድ ስራው መጠሪያ በማድረግ ማስመዝገብና መንቀሳቀስ ማለት ነው፡፡

አንድ ግለሰብ በንግድ ስም መዝገብ መመዝገብ ሳያስፈልገው በራሱ ስም በቀጥታ የንግድ ምዝገባ በማድረግ ወደ ንግድ ስራ እንቅስቃሴ መግባት የሚችል ሲሆን የንግድ ስራ ስም ለማስመዝገብና ለመንቀሳቀስ ግን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ ይኖርበታል፡፡

አጠቃላይ የአገልግሎቱ የአሰራር መመሪያ

 • የንግድ ስሙ የንግድ ስራውን ዘርፍ  በESIC ኮድ መሰረት የግሩፑን/የንዑስ ግሩፑን/የዲቪዥኑን መደብ  ለይቶ የሚጠቅስ  መሆን አለበት
 • የመሰኩ አጠቃላይ መጠሪያ ወይንም የወል ስም ብቻ መሆን የለበትም
 • የንግድ ስም ወይንም የንግድ ማህበር መጠሪያ የንግዱን ዓይነት ወይንም  ከላይ የተመለከተውን የሥራ መስክ ለይቶ ማመልከት አለበት
 • የንግድ ስሙ ከፌደራል ፣ ከክልል መንግስታት ፣አስፈጻሚ አካላት ባለስልጣን መ/ቤቶች ወይም ኤጀንሲዎች ፣ከማዘጋጃ ቤቶች ወይም የቀበሌ መስተዳድሮች ፣ከመከላከያ እና ፖሊስ ድርጅቶች ጋር ያልተያያዘ መሆን አለበት
 • ከሌሎች ሀገራት፣አለም አቀፍ ወይም አህጉራዊ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ ስሞች መሆን የለባቸውም
 • ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ፣ድርጅት ወይም ማህበረሰብ፣ ጎሳ፣ የሰራተኛ ማህበራት እና የህብረት ስራ ማህበራት ጋር የተያያዘ መሆን የለበትም
 • የአገር መሪዎች፣ የታላላቅ ታዋቂ ሰዎችና የዓለም ትላልቅ ከተሞች  ስሞች ለንግድ ስም ሊውሉ አይችሉም
 • የንግድ ስም የሁለት ሀገሮችን ስሞች በአንድነት(ለምሳሌ ኢትዮ ካናዳ) የያዘ መሆን የለበትም
 • የንግድ ስም በምህጸረ ቃል ሲሆን ትርጉም ያለው ሆኖ ቃላቱ የባለቤቱን ወይንም የቤተዘመዱን ወይንም የባለ አክሲዮኖችን ፊደላት ብቻ መያዝ አለበት
 • በሌላ አገር የተመዘገበ ኩባኒያ አዲስ በሚመሰረት የንግድ ማህበር ባለአክሲዮን በሚሆንበት ጊዜ አዲሱ መጠሪያ የአባል ኩባንያው ስም መሆን አይኖርበትም
 • በንግድ ስሙ ሆልዲንግስ፣ግሩፕ፣አሶስየት፣ፓርትነርስ፣ የመሳሰሉ ቃላት መጨመር የለባቸውም
 • በነባር የንግድ ስሞች ላይ ከፊትና ከኋላ ሌላ ቃላት በመጨመር የንግድ ስም አይሰጥም
 • የንግድ ስሙ ከሌላ የንግድ ስም ጋር የሚመሳሰል ድምጽ (PRETENTIOUS SOUNDING) ሊኖረው አይገባም
 • ከሚሰጡ የንግድ ስራ አይነቶች ከምርት ወይም አገልግሎት ባህሪይ ጋር ቀጥታ ተዛማጅነት ያላቸው ገላጭ ቃላት መሆን የለባቸውም
 • የሚያሳስቱ እና የባለቤትነት  ግጭት የሚፈጥሩ መሆን የለባቸውም
 • ሰብአዊነትን የሚያንኳስሱ እና የሚያንቋሽሹ መሆን የለባቸውም
 • በሌላ ቋንቋ ተመሳሳይ ትርጉም ካላቸው የተመዘገቡ ስሞች ጋር ተመሳሳይ መሆን የለባቸውም
 • ከባህል ፣ከሃይማኖት እና ከመንግስት ፖሊሲ ጋር የሚጋጩ፣የሚያንቋሽሹ  መሆን የለባቸውም

የሚጠየቁ መስፈርቶች

 • የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ስያሜ እዲሰጠው/እንዲሰጣቸው የቀረቡ የንግድ ስራ ፍቃድ/ፍቃዶች ፎቶ ኮፒ
 • አመልካቹ የራሱንየቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ከፎቶ ኮፒጋር፤በተጨማሪም ጉዳዩን የሚያስፈፅመው ሰው ወይንም አመልካቹ ስራ አስኪያጅ ካልሆነ በውልና ማስረጃ የፀደቀ የውክልና ደብዳቤ
 • ስደስትወርያልሞላውሁለትየስራ እስኪያጁጉርድፎቶግራፍ፤
 • የንግድ ስሙ እንዲጣራ የሚሞላውን ፎርም መሙላት

ዝርዝር የአገልግሎቱ ሂደት

 • የቀረበው የንግድ ስም ከላይ በቀረቡት መስፈርቶች መሰረት  መሆኑን ማረጋገጥ
 • የቀረቡት  የንግድ ስራ ስም ጥያቄዎች በመረጃ ቋት ውስጥ በሌላ ያልተያዙ መሆኑን ማረጋገጥ
 • የተያዙ ከሆነ ሌላ አማራጭ የንግድ ስራ ስም እንዲያቀርቡ ማድረግ
 • የግለሰብ ስም ከሆነ እስከ ቅድም አያት ድረስ በመመዝገብ የተለየ መሆኑን ማረጋገጥ
 • ስሙ በጋዜጣ እንዲወጣ ለ ፕሬስ ድርጅት ደብዳቤ መፃፍና መላክ
 • ከ 15 ቀን በኋላ በቀረበው የንግድ ስም ላይ ተቃዋሚ ካልቀረበ  የጋዜጣውን ሁለት ቅጂ በመያዝ የምስክር ወረቀት አትሞና ፈርሞ መስጠት
 • በዚሁ መሰረት የንግድ ስራ ስም ምዝገባውን በማጽደቅ ከንግድ ስራ ምዝገባ ጋር በአንድነት ማከናወ